የሀገር ውስጥ ዜና

ጀግኖች አባቶቻችን በክብር ያቆዩልንን ሀገር በቀላሉ ለማፍረስ የሚጥሩ አካላት ምናልባትም የአድዋን ድል ምንነት ያልተገነዘቡ ናቸው-አቶ እርስቱ ይርዳ

By Feven Bishaw

March 01, 2022

አዲስ አበባ፣የካቲት 22፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጀግኖች አባቶቻችን በክብር ያቆዩልንን ሀገር በቀላሉ ለማፍረስ የሚጥሩ አካላት ምናልባትም የአድዋን ድል ምንነት ያልተገነዘቡ መሆናቸውን የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ እርስቱ ይርዳ ተናገሩ፡፡

ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ 126ኛውን የአድዋ ድል በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡