አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ተታለው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ የኬንያን ድንበር በህገወጥ አቋርጠው የገቡ 139 ኢትዮጵያውያንን ሚሲዮኑ በምህረት ክሳቸው ተቋርጦና ከእስር ቤት ተፈተው ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ ድጋፍ አድርጓል።
ኢትዮጵያውያኑ በኪያምቡ፣ ጊጊሪ፣ ፓንጋኒ፣ ጆጎ፣ ቡሩቡሩ እና ዳንዶራ እስር ቤቶች በእስር ከአንድ እስከ ዘጠኝ ወር ድረስ የቆዩ ናቸው።