የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ የዐድዋ ድል በዓል በሰላም መከበሩን ፖሊስ አስታወቀ

By Meseret Awoke

March 02, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በልዩ ልዩ ፕሮግራሞች የተከበረው 126ኛው የዐድዋ የድል በዓል በሰላም መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የዐድዋ ድል 126ኛው በዓል በከተማዋ በዳግማዊ አፄ ምኒልክ አደባባይ እና በዐድዋ ድልድይ በደማቅ ስነ ስርዓት በሰላም እንዲከበር ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የሚጠበቅበትን ተግባር ማከናወኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ከማለዳው ጀምሮ በዓሉ ወደሚከበሩባቸው ስፍራዎች የተጓዙት የመዲናዋ ነዋሪዎች ለፀጥታ አካላት ባሳዩት ተባባሪነት እና ባደረጉት ድጋፍ ለበዓሉ በሰላም መጠናቀቅ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጿል፡፡

ሃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡት የፀጥታ አካላት እና በተለያየ መልኩ የፀጥታውን ስራ ለደገፉ በጎ ፈቃደኞች እንዲሁም ለመላው የከተማዋ ነዋሪዎች የአዲስ አበባ ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል፡፡

በተያዘው የበጀት ዓመት የተከበሩ ሃይማኖታዊ እና ብሔራዊ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ህብረተሰቡ ከፍተኛ ሚና ማበርከቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውሶ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!