አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ምክር-ቤት ከነገ ጀምሮ የ3ኛ የስራ ዘመን 1ኛ አመት 50ኛ መደበኛ ጉባኤን ያካሂዳል፡፡
የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ፈትህያ አደን የምክር-ቤቱን 50ኛ መደበኛ ጉባኤ አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለጹት፥ ምክር ቤቱ በሁለት ቀናት ቆይታው የአስተዳደሩን የአስፈፃሚ አካላት የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ እንደሚያፀድቅ ገልፀዋል።