ዓለምአቀፋዊ ዜና

በጦርነቱ ምክንያት ከዩክሬን ወደ ጎረቤት ሀገራት ለመሻገር የሚሞክሩ አፍሪካውያን የዘረኝነት ተጽእኖ እየደረሰብን ነው አሉ

By Meseret Awoke

March 02, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ – ዩክሬን ጦርነትን በመሸሽ ከዩክሬን ወደ ተለያዩ ጎረቤት ሀገራት ለመሻገር የሚሞክሩ አፍሪካውያን በቆዳ ቀለማቸው ምክንያት ተጽእኖ እየደረሰባቸው መሆኑን ተናገሩ።

ጦርነቱን በመሸሽ ከዩክሬን ወደ ተለያዩ ጎረቤት ሀገራት ለመሸሽ በሞከሩ አንዳንድ አፍሪካውያን ላይ የዘረኝነት ጥቃት እየተፈጸመባቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ኢስቲዋኒያት የሆነችው ቭክሌ ድላምኒ ከዩክሬን ወደ ሮማንያ ለመሻገር ባደረገችው ጉዞ እጅግ ፈታኝ የዘረኝነት ተጽእኖዎች እዳስተናገደች ትናገራለች፡፡

ፖሊሶች መሳሪያ በመደገን የማስፈራራት ድርጊት እስከመፈጸም የሚደርስ ተጽእኖ አድርሰውብናል ብላለች፡፡

ናይጄሪያዊው ቪክቶር ኤልድረድ በበኩሉ ከልቪቭ ለመውጣት ሙከራ ስናደርግ ለዩክሬናውያን ብቻ ባቡር ተፈቅዶ እኛ ግን ባቡር በመከልከላችን በአስቸጋሪ የአየር ፀባይ ለብዙ እንግልት ተዳርገን ቆይተን ይላል።

አያይዞም በራሳችን መንገድ ከዩክሬን መውጣት ችለናል ሲል ጉዞው ለአፍሪካውያን ምን ያህል ፈታኝ እንደነበር ያስረዳል፡፡

ረዥሙን እና አስቸጋሪውን ጉዞ ተቋቁመን ስሎቫኪያ ብንደርስም የናይጀሪያ መንግስት አሁንም ድረስ ምንም እገዛ አላደረገልንም ሲልም ተናግሯል፡፡

በዩክሬን የሚማሩ አፍሪካውያን ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ይነገራል፤ ከሌሎች አህጉራት ተማሪዎች ጋር ሲነጻጸር ቁጥራቸው 20 በመቶ እንደሚሸፍን አናዶሉ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!