የሀገር ውስጥ ዜና

ኤምባሲው በዩክሬን ለሚገኙና ከዩክሬን ወደ ፖላንድና ሌሎች አጎራባች አገሮች በመሄድ ላይ ላሉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ማግኘት የሚችሉበት ሊንክ ይፋ አደረገ

By Feven Bishaw

March 02, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዩክሬን ለሚገኙና ከዩክሬን ወደ ፖላንድና ሌሎች አጎራባች አገሮች በመሄድ ላይ ላሉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ማግኘት የሚችሉበት ሊንክ ይፋ አድርጓል፡፡

ኤምባሲው በሩስያ እና ዩክሬን መካከል በተፈጠረው ጦርነት ምከንያት ዜጎች ወደ አጎራባች አገራት ለመግባት በሚያደርጉት ጥረት ከአገራቶቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስርያ ቤቶች ጋር በመተባበር በተቻለ መጠን ያለችግር ማቋረጥ እንዲችሉ ሲሰራ መቆየቱን አንስቷል፡፡