የሀገር ውስጥ ዜና

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ 9ኛ ዓመት በዓለ ሢመት እየተከበረ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

March 03, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ 9ኛ አመት በዓለ ሢመት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እየተከበረ ነው፡፡

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትረያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት 9ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት እየተከበረ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በበዓለ ሢመቱ የኃይማኖት አባቶች እና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!