የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ የአሴካ ጉባኤን በምክትል ፕሬዚዳንትነት እንድትመራ ተመረጠች

By ዮሐንስ ደርበው

March 03, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የአፍሪካና የዐረቡ ዓለም የምክር ቤቶች፣ ሹራዎች፣ እና አቻ ምክር ቤቶች ማህበር ኮንፍረንስ (አሴካ) ጉባኤን በምክትል ፕሬዚዳንትነት እንድትመራ በጉባኤው መመረጧን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ገለጸ፡፡

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር የተመራው የልዑካን ቡድን በሞሮኮ ራባት እየተካሄደ ባለው በ9ኛው የአሴካ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ከተለያዩ የአፍሪካ እና የአረቡ ዓለም ሀገራት የተውጣጡ ተሳታፊዎች በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል ነው የተባለው።

አቶ አገኘሁ ተሻገር በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ስለአየር ንብረት ለውጥ፣ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ፣ ታላቁ የህዳሴ ግድብና የጋራ ተጠቃሚነት እንዲሁም በአፍሪካና በአረቡ ዓለም ሀገራት መካከል ሊኖር ስለሚገባው ነጻ የንግድ ቀጠና እና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል፡፡

የአሴካ ጉባኤን በምክትል ፕሬዚዳንትነት መድረኩን እንዲመሩ በጉባኤው በመመረጣቸው መድረኩን እየመሩ እንደሚገኙ ከፌደሬሽን ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር የአሴካ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ሞሮኮ ዋና ከተማ ራባት መግባታቸው ይታወቃል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!