የሀገር ውስጥ ዜና

በዐቃቤ ሕግ ክስ የተመሰረተበት ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው በነጻ ተለቋል በሚል የሚናፈሰው ወሬ መሰረተቢስ ነው

By Feven Bishaw

March 05, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዐቃቤ ሕግ ክስ የተመሰረተበት ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው በነጻ ተለቋል በሚል የሚናፈሰው ወሬ መሰረተ ቢስ መሆኑን የፍትሕ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ በተለያዩ የክስ መዝገቦች በሙስና ወንጀል በዐቃቤ ሕግ ክስ የተመሰረተበት ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው በነጻ ተለቋል በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ገልፆ መዛግብቶቹ ገና በክርክር ሂደት ላይ የሚገኙ እና የተከሳሽን መከላከያ ምስክር ለመስማት የተቀጠሩ መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡