የሀገር ውስጥ ዜና

ለተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት ሁልጊዜም ከፍ ያለ ምስጋና አለው- አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር

By Feven Bishaw

March 07, 2022

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አንዳንድ የውስጥና የውጭ ኃይላት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ ለመጣል ባሰፈሰፉበት ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን ከቆሙት ጥቂት ሀገራት መካከል አንዷ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ በመሆኗ የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት ሁልጊዜም ከፍ ያለ ምስጋና አለው ሲሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ::

በ11ኛው የአፍሪካና የዐረቡ ዓለም አፈ ጉባዔዎችና አቻ ምክር ቤቶች የጋራ ጉባዔ (አሴካ) ላይ የተሳተፉት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር ከጉባዔው ጎን ለጎን ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የፌዴራል ብሔራዊ ምክር ቤት አፈጉባዔ ሳክር ሆባሽ ጋር ተወያይተዋል::