የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በስልክ ተወያዩ

By Meseret Awoke

March 08, 2022

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከተመድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በስልክ ተወያዩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጦርነት ወደ ተጎዱ አካባቢዎች ሰብዓዊ አቅርቦት ማድረስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከአንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር በስልክ መክረዋል፡፡

አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ÷ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ መግባባት ላይ ለመድረስ ውይይት በሚጀመርበት ሁኔታ ላይም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መወያየታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!