የሀገር ውስጥ ዜና

ስዊድን ለአፍሪካ የስነተዋልዶ ጤና አጠባበቅ ስትራቴጂ የሚውል ከ50 ሚሊየን ዶላር በላይ ድጋፍ አጸደቀች

By Meseret Awoke

March 08, 2022

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የስዊድን መንግስት ለአፍሪካ የስነተዋልዶ ጤና አጠባበቅ ስትራቴጂ የሚውል ከ50 ሚሊየን ዶላር በላይ ድጋፍ አጸደቀ።

የስዊድን መንግሥት በአፍሪካ ሀገራት ከፈረንጆቹ 2022 እስከ 2026 የሚያከናውነውን የስነተዋልዶ ጤና አጠባበቅና የጾታ ትንኮሳ መከላከልን የሚያግዝ አዲስ ስትራቴጂ ነድፏል።

በዚህም የሀገሪቱ መንግስት ለስትራቴጂው ተደራሽነትና በዘርፉ ለሚከናወኑት ስራዎች ተጨማሪ 500 ሚሊየን የስዊድን መገበያያ ገንዘብ ክሮና ወይም ከ50 ሚሊየን 735 ሺህ ዶላር በላይ ድጋፍ ማጽደቁ ተገልጿል።

አሁን የጸደቀው ድጋፍ የስዊድን መንግስት የሚያከናውናቸውን የሰብአዊ መብት ጥበቃ ተግባራትን እንደሚያግዝ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!