የሀገር ውስጥ ዜና

ከመጪው የዝናብ ወቅት አስቀድሞ ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዝግጅት እናድርግ – ጠ/ሚ ዐቢይ

By Alemayehu Geremew

March 10, 2022

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከመጪው የዝናብ ወቅት አስቀድሞ ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በመላ ሃገሪቱ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ አስገነዘቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ክረምት ሳይገባ ለዘንድሮው የአረንጓዴዐሻራ መርሐ ግብር የዝናብ ውኃ ለማቆር እና የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት እጅግ ተስፋ ሰጪ መሆኑን አስታውቀዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ለአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከመጪው የዝናብ ወቅት አስቀድሞ በቂ ዝግጅት ማድረግ ይገባል ብለዋል።