የሀገር ውስጥ ዜና

አዋሽ የውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት በሜካናይዝድ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ባለሙያዎች አስመረቀ

By Feven Bishaw

March 11, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዋሽ የውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት በተለያዩ የሜካናይዝድ ሙያዎችና በከባድና ቀላል መኪና አሽከርካሪነት ያሰለጠናቸውን ባለሙያዎች አስመርቀ፡፡

በዝግጅቱ ላይ የምድር ሀይል ጠቅላይ መምሪያ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀነራል እንዳልካቸው ወልደኪዳን፣ የማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ተመስገን አቦሴን ጨምሮ ከፍተኛ ወታደራዊና የአካባቢው የመስተዳደር አካላት ተገኘተዋል።