አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ፓርቲ ጉባዔ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን መረጠ።
አንደኛ ጉባዔውን ያካሄደው የብልፅግና ፓርቲ የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮች መፍታት የሚችሉ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን መርጧል።
የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ በሰጡት መግለጫ፥ 225 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ተመርጠዋል።
የኮሚቴው አባላት ሲመረጡም በኢትዮጵያዊነት እና በኢትዮጵያ አንድነት የማይደራደር፣ የኢትዮጵያውያንን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት የሚያጎላ፣ ብዝሀነትን የሚቀበል፣ ኢትዮጵያ የገጠማትን ዘርፈ ብዙ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ችግሮች ለመፍታት ዕውቀቱ፣ ቁርጠኝነቱ እና ሥነ ልቡና ያለው፣ ሌብነትን አምርሮ የሚታገል እንዲሁም ጽንፈኝነትንና አክራሪነትን የሚቃወም የሚሉት በመስፈርትነት ታይተዋል።
የፓርቲው ጉባዔ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ከመረጠ በኋላ የተመረጡት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን የመረጡ ሲሆን፥ በዚህም መሠረት፦
1. ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ 2. አቶ አደም ፋራህ 3. አቶ ደመቀ መኮንን 4. አቶ ደስታ ሌዳሞ 5. ዶ/ር ፍጹም አሰፋ 6. አቶ አብርሃም ማርሻሎ 7. አቶ አሻድሊ ሀሰን 8. አቶ ጌታሁን አብዲሳ 9. አቶ ኡሙድ ኡጁሉ 10. አቶ ተንኳይ ጆክ 11. አቶ ኦርዲን በድሪ 12. አቶ አሪፍ መሃመድ 13. ዶ/ር አብርሃም በላይ 14. ዶ/ር ሊያ ታደሰ 15. ሀጂ አወል አርባ 16. ሀጅሊሴ አደም 17. አቶ ኤሌማ አቡበከር 18. ወ/ሮ ሀሊማ ሀሰን 19. አቶ ሙስጠፌ መሀመድ 20. አቶ አህመድ ሽዴ 21. ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ 22. አቶ ፀጋዬ ማሞ 23. ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል 24. አቶ ተስፋዬ በልጅጌ 25. አቶ ርስቱ ይርዳው 26. አቶ ተስፋዬ ይገዙ 27. አቶ ሞገስ ባልቻ 28. አቶ ጥላሁን ከበደ 29. አቶ መለሰ ዓለሙ 30. አቶ ሽመልስ አብዲሳ 31. አቶ ፍቃዱ ተሰማ 32. ዶ/ር አለሙ ስሜ 33. ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ 34. አቶ አወሉ አብዲ 35. አቶ ሳዳት ነሻ 36. ወ/ሮ አዳነች አቤቤ 37. ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ 38. ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ 39. ዶ/ር ይልቃል ከፍያለ 40. ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ 41. አቶ ተመስገን ጥሩነህ 42. አቶ መላኩ አለበል 43. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ 44. ዶ/ር ሰማ ጥሩነህ 45. አቶ ግርማ የሺጥላ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በመሆን ተመርጠዋል።
በአልአዛር ታደለ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!