ዓለምአቀፋዊ ዜና

ኔቶ በዩክሬን ግጭት ውስጥ ገባ ማለት 3ኛው የዓለም ጦርነት ተጀመረ ማለት ነው- ቻርለስ ሚሼል

By Feven Bishaw

March 14, 2022

አዲስ አበባ፣መጋቢት 5፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን አገሮች ድርጅት ( ኔቶ) በዩክሬን ግጭት ውስጥ ከገባ 3ኛው የዓለም ጦርነት ተጀመረ እንደማለት ነው ሲሉ የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ቻርለስ ሚሼል ተናገሩ፡፡

የኅብረቱ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ዛሬ ለንባብ ለበቃው ኤል ፔስ የተሰኘ የስፔን ታዋቂ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ፥ የአውሮፓ አገሮች በዩክሬን እና ሩሲያ ግጭት ውስጥ መግባት የለባቸውም ብለዋል፡፡