አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባን የሚወክሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከመረጣቸው ህዝብ ጋር ለመወያየት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ጋር ተወያዩ።
ተወካዮቹ እንዳሉት ፥ የተገኙ ድሎች እና ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት ከመራጩ ህዝብ ጋር ተቀራርቦ መወያየት እጅግ አስፈላጊ ነው።
የአዲስ አበባ የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለስ አለሙ በበኩላቸው ፥ ፓርቲው የከተማው ተመራጮች ከመረጣቸው ህዝብ ጋር በየሶስት ወሩ የሚገናኙበት አሰራር መፈጠሩን ገልፀዋል፡፡
በዚህ ዙር የተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሚያደርጉትን ውይይት የተሳካ ለማድረግና መራጩ ህዝብ የሚያነሳቸውን ችግሮች በጋራ ለመፍታት ፓርቲው ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል።
ተወካዮቹ በቀጣይ ቀናቶች በቀጥታ ከመረጣቸው ህዝብ ጋር በመገናኘት ህዝቡ በሚያነሳቸው የተለያዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ላይ በመወያየት እልባት የሚያገኘበትን መንገድ ለማመቻቸት እንደሚሠሩ መግለጻቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!