አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ምዕራብ ጎዴይ ፕሮጀክት በ1 ሺህ 804 ሄክታር መሬት ላይ የእንስሳት መኖና የምግብ ሰብል ማልማት መቻሉን የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ አህመድ አብዲ ገለጹ፡፡
በክልሉ የተከሰተውን የድርቅ አደጋ ለመቋቋም በሸበሌ ዞን ቤርዓኖ ወረዳ በምዕራብ ጎዴይ ተፋሰስ ፕሮጀክት ላይ የለሙ የእንስሳት መኖ እና የምግብ ሰብልን ለመሰብሰብ ጊዜው መድረሱን ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል።