የሀገር ውስጥ ዜና

የክልሉ ካቢኔ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

By Meseret Awoke

March 17, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ “የቤኒሻንጉል ጉሙዝ የልማት ድርጅት (የቤጉ ዴቨሎፕመንት ግሩፕ)” የተሰኘውን የመንግስት የልማት ድርጅት እንዲቋቋም በቀረበው አጀንዳ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በዚህም መሠረት የቤጉ የልማት ድርጅት በኮንስትራክሽን፣ በማዕድን፣ በግብርናና በጥናት ዲዛይን ዘርፎች በክልሉ ያለውን ዕምቅ የተፈጥሮ ሃብት በራሱ እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ጥምረት በመፍጠር በክልሉ የሚታዩ የልማት ክፍተቶችን እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ታምኖበት ፈጥኖ ወደሥራ እንዲገባ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!