አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዋግ ኸምራ ዞን በቤላ ተራራ ላይ የተከሰተውና አምስተኛ ቀኑን ያስቆጠረው የእሳት ቃጠሎ አደጋ ወደ ሌላ ቦታ እንዳይዛመት የመከላከል ስራ እየተሰራ መሆኑን የአማራ ክልል የአካባቢ የደን እና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
ሰደድ እሳቱን ለመከላከል እና ቃጠሎው ወደ ሌላ እንዳይዛመትና ከፍተኛ ውድመት እንዳያስከትል በአካባቢው ማህበረሰብና በባለድርሻ አካላት የመከላከል ስራ እየተሰራ ነው፡፡
በተጨማሪም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከፌደራል ደን ኮሚሽን ጋር ችግሩን ሙሉ በሙሉ ለማስቆም ጥረት እንዲደረግና አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሠጥ ጥያቄዎች ቀርበው ኮሚሽኑ ችግሩን ለመፍታት የድርሻውን እንዲወጣ መግባባት ተችሏል ነው የተባለው።
ሰደድ እሳቱ ከተከሰተ ቀን ጀምሮ ከ100 ሔክታር በላይ የሚሸፍን ብዝሐ ህይወት እና የተፈጥሮ ጥብቅ ደን መውደሙን የዞኑ የአካባቢና ደን ጥበቃ አስታውቀዋል፡፡
የቤላ ተራራ የብሌን ብሔረሰብ እትብት የማንነት አሻራን አቅፎ የያዘ ፤ በሰሜን የዳህላ ተፋሰስ ፣ የቤላ ፣ የወለህና ዲባ ወንዝ ፣ በምስራቅ የአሏቅ ወንዝ ፣ በምዕራብ የተላ ባርግባ ወንዝ ፤ እንዲሁም በደቡብ የተራራው አቅጣጫ የጅውና ገብርኤል ፣ የአግጣ ጊዮርጊስና የወይላ ወንዝ መነሻ ምንጭ በመሆን የሚያገለግል የውሀ ጋን በመባል የሚታወቅ ተፈጥሯዊ ተራራ መሆኑ ይታወቃል ።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!