የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ከመጋቢት 15 ቀን ጀምሮ ይካሄዳል

By Feven Bishaw

March 18, 2022

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት ከመጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛ ጉባዔውን እንደሚያካሂድ የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬ አስታውቀዋል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ ምክር ቤቱ ስለሚያደረግው መደበኛ ጉባኤ መግለጫ ሰጥተዋል። ምክር ቤቱ ስድስተኛ ዙር አንደኛ ዓመት ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔውን ነው የሚያካሂደው።