አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዩክሬን የተካሄደ ያለው የሩሲያ ወታደራዊ ዘመቻ ዋና ዓላማ ዶንባስን ከዘር ማጥፋት ወንጀል ነፃ ማውጣት ነው ሲሉ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተናገሩ፡፡
ፕሬዚደንቱ በሉዚን ስታዲየም ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፥ሩሲያ ያካሄደችው ወታደራዊ ዘመቻ ዋና ዓላማ የዶንባስ ግዛት በሆኑት የዶኔስክ እና ሉጋነስክ ግዛቶች ላይ የሚፈፀሙ የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን ለመከላከል ነው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በአውሮፓውያኑ 2014 ወደ ስልጣን በመጡት የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቭሎዶሚር ዘነልስኪ ላይ ተቃውሞ ያላቸው የዶንባስ ነዋሪዎች ድብድባ፣ የተለያዩ በዘረኝነት ላይ የተመሰረቱ ክልከላዎች፣ የአየር ጥቃቶች እንዲሁም ሰውር ግድያ ሲፈፀምባቸው እንደቆዩ ነው ፑቲን የተናገሩት፡፡
የዚህ ጉዳይ አስፈፃሚ የሆነው የዩክሬን ወታደራዊ ኃይል እእየተደመሰሰ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ ፑቲን፥ በዶንባስ በተፈፀሙ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች የተሳተፉ አካላትም ተጠያቂ እንዲሆኑ እናደርጋለን ብለዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ 24 ቀናት ባሰቆጠረው የዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር እነወያይ የሚል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ፕሬዚደንት ዘለንስኪ በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ከፑቲን ጋር ለመገናኘት እና ስለ ዩክሬን የግዛት አንድነት እና ፍትሃዊነት ለመምክር እንደሚፈልጉ መግለፃቸውን ስፑትኒክ ኒውስ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!