ዓለምአቀፋዊ ዜና

በቻይና 133 ዜጎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውሮፕላን ተከሰከሰ

By Melaku Gedif

March 21, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና 133 የሚሆኑ መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውሮፕላን መከስከሱ ተሰምቷል፡፡

ባለቤትነቱ የምስራቅ ቻይና አየር መንገድ የሆነው ይህ አውሮፕላን፥ ጉዋንግዚ ጉዋንግ በተሰኘ ክልል ነው የተከሰከሰው፡፡

አውሮፕላኑ በተራራ ላይ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ ምክንያት ሳይከሰከስ እንዳልቀረ ሲጂቲኤን በዘገባው ጠቁሟል፡፡

አውሮፕላኑ 133 ሰዎችን አሳፍሮ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን÷ እስካሁን በአደጋው የደረሰው ጉዳት አለመታወቁ ተመላክቷል፡፡

አሁን ላይም አደጋው በተከሰተበት አካባቢ የነፍስ አድን ሰራተኞች መሰማራታቸው ታውቋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ! ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!