የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ግርማ ዋቄ የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ግሩፕ የማኔጅመንት ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ

By Mekoya Hailemariam

March 23, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ለብዙ ዓመታት ያገለገሉት አቶ ግርማ ዋቄ የአየር መንገዱ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በቅርቡ መሾማቸውን አየር መንገዱ አስታወቀ፡፡

አቶ ግርማ ዋቄ አየር መንገዱን ለሰባት ዓመታት በመምራት ለዕድገት እንዲበቃ መሰረት የጣሉ፣ በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ የስራ ልምድ ያላቸውና በዘርፉ ስኬታማ መሪ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

አቶ ግርማ ዋቄ የአየር መንገዱ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መሾማቸው አየር መንገዱን ለበለጠ ስኬት ሊያበቁ የሚችሉና ተቋሙ ወደፊት ከሚጠበቅበት የዕደገት ደረጃ ሊያደርሱት እንደሚችሉም የታመነ መሆኑንም አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም በሚሰጡት በሳል አመራርና ትክከለኛ ውሳኔ ሰጭነት ውጤታማ መሆናቸውን በተግባር ያረጋገጡ መሆናቸውም ተመልክቷል፡፡

አቶ ግርማ ዋቄ ከወጣትነት ዕድሜያቸው ጀምሮ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተምረውና አድገው በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ለ34 ዓመታት አገልግለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም አቶ ግርማ በመካከለኛው ምስራቅ የገልፍ አየር መንገድንና ዲኤቾ ኤል ኩባንያንም በኃላፊነት አገልግለዋል፡፡

በአውሮፓውያኑ 2004 የኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው አየር መንገዱን ለሰባት ዓመታት ያህል በዋና ስራ አስፈጻሚነት በመምራት ለዕድገት አብቅተውታል፡፡

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ከለቀቁ በኋላም በተለያዩ አገራት የአየር መንገድ ከፍተኛ አመራርና የአየር ትራንስፖርት ጉዳዮች አማካሪ ሆነው አገልግለዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!