ከንቲባ አዳነች አቤቤ በፊርማ ስነ ስርዓቱ ወቅት እንደገለጹት÷ ዛሬ የተካሄደው ስምምነት ለይስሙላ የሚደረግ ሳይሆን አስፈጻሚውን አካል ለመቆጣጠር የሚያስችል ዓላማ ያነገባና ስራን በተገቢው መንገድ ለማከናወን የሚያስችል ነው፡፡
ምክር ቤቱና ሕዝባችን የጣለሉብንን ኃላፊነት በተሟላ አግባብ እንድንፈጽም የሚያስችል የተጠያቂነት ስርዓትን ከንግግር ባለፈ መሬት ላይ ለማውረድ የሚረዳ፤ የተሻለ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ እንድናቀርብ የሚያስችለንም ነው ብለዋል፡፡
ዛሬ በተፈረመው ስምምነት መሰረት የሕዝብ ተወካዮች አስፈፃሚውን አካል በየጊዜው በመከታተል፥ በመቆጣጠርና በመደገፍ የከተማዋን ዕድገት፣ የሕዝቡን ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ ሊሠሩ እንደሚገባ መናገራቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡