የሀገር ውስጥ ዜና

ቤተክርስቲያኗ በጦርነቱ የተጎዱ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የ135 ሚሊየን ብር ኘሮጀክት ይፋ አደረገች

By Feven Bishaw

March 25, 2022

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በጦርነቱ የተጎዱ ከ227 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የ135 ሚሊየን ብር ኘሮጀክት ይፋ አደረገች ፡፡

ቤተክርስቲያኗ በትግራይ፣ አማራ፣ አፋርና ኦሮሚያ ክልሎች በጸጥታ ችግር እና ጦርነት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ሰብዓዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም የሚውል ኘሮጀክት ነው ዛሬ ይፋ ያደረገችው።