የሀገር ውስጥ ዜና

ሶማሌ ክልል ከለውጡ በፊት ከነበረበት የጸጥታ ችግር ወጥቶ ባለፉት 3 ዓመታት ያረጋገጣቸው ውጤቶች የሚደነቁ ናቸው – ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ

By Meseret Awoke

March 25, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሶማሌ ክልል ከለውጡ በፊት ከነበረበት የጸጥታ ችግር ወጥቶ ባለፉት 3 ዓመታት ያረጋገጣቸው ውጤቶች የሚደነቁ መሆናቸውን የከተማና የመሠረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ገለጹ፡፡

የከተሞች ተቋማዊና የመሠረተ ልማት ፕሮግራም የልምድ ልውውጥ መድረክ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ እና የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒን ጨምሮ ሌሎች የክልልና ከተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የተውጣጡ የከተማ አስተዳደር አመራሮች ተሳትፈዋል።

ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ፥ ክልሉ ከለውጡ በፊት ከነበረበት የሰላምና የፀጥታ ችግር ወጥቶ በክልሉ መንግስት በሳል አመራር የተመዘገቡ ወጤቶች የሚደነቁ መሆናቸውን ተናገረዋል።

የከተሞች ተቋማዊና የመሠረተ ልማት ፕሮግራም በከተሞች በርካታ ለውጦች እያመጣ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሯ ፥ የልምድ ልውውጥ መድረኩ በክልሉና በተለያዩ ከተሞች በፕሮግራሙ የተሰሩ ስራዎችን በመገምገም መልካም ተሞክሮዎች የሚወሰድበት መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ሙስጠፌ በበኩላቸው፥ ከተሞች ርቀው ሳይሄዱ እዚሁ ያላቸውን መልካም ተሞክሮዎች በመለወጥ ልማትና እድገትን ለማፋጠን የልምድ ልውውጥ መድረኮች የሚያበረክቱት አስተዋኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

በከተሞች እያደገ ለመጣው ህዝብ ጥራት ያለው አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በክልሉ ባለፉት ሶስት ዓመታት በከተሞች መንገድ ፣ ውሃ፣ መብራትና ሌሎች አገልግሎቶችን ለማስፋፋት ሰፊ ስራ እንደተሰራ መናገራቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!