አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስትታ ባለሥልጣን (ኢጋድ) የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትን ለማሳለጥ ይቻል ዘንድ ግጭት ለማቆም በመወሰኑ አድናቆቱን ገልጿል።
የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ፥ የኢትዮጵያ መንግስት ሰብዓዊ ዕርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የሚላከውን አቅርቦት ለማሳለጥ እንዲቻል ግጭትን ለማቆም ያስተላለፈው ውሳኔ ተቀባይነት ያለው እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል።