የሀገር ውስጥ ዜና

በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ ትራፊክ አደጋ ሕፃን ልጅን ጨምሮ የሰዎች ህይወት አለፈ

By Feven Bishaw

March 25, 2022

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከደሴ ወደ ሰቆጣ ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ አንድ ህጻን ልጅን ጨምሮ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ተሳፋሪዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 37 ተሳፋሪዎች ቆስለው ላሊበላ ሆስፒታል መግባታቸው ተነገረ።

ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ ከደሴ ከተማ ተነስቶ ወደ ሰቆጣ ሲጓዝ የነበረና ከ43 ሰው በላይ የጫነ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላሊበላ ከተማን አለፍ ብሎ ሰኞ ገበያ ከምትባል አካባቢ በመገልበጡ አደጋው መድረሱን ከዋግ ኸምራ ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡