የሀገር ውስጥ ዜና

በ40 ቀናት ውስጥ በ10 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ልዩ ትምህርት ቤት ተመረቀ

By Meseret Awoke

March 26, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ዞን ሸቤ ሶምቦ ወረዳ በ40 ቀናት ውስጥ ግንባታው የተጠናቀቀው ልዩ ትምህርት ቤት ተመረቀ።

በኦሮሚያ ልማት ማህበር 10 ሚሊየን ብር በሆነ ወጪ ከ40 ቀናት በፊት ግንባታው የተጀመረው የሸቤ ልዩ ትምህርት ቤት በዛሬው ዕለት የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አባዱላ ገመዳ በተገኙበት ተመርቋል።

በጅማ ዞን የሸቤ ሶምቦ ወረዳ እንደ ክልል ብዙ ተማሪዎችን ወደ አዳሪ ትምህርት ቤት በማስገባት የላቀ አፈፃፀም ማስመዝገቡን ተከትሎ ተገንብቶ ለወረዳው ህዝብ የተበረከተ መሆኑን አቶ አባ ዱላ ገመዳ ገልፀዋል።

ትምህርት የሁሉም ነገር መሰረት መሆኑን የተናገሩት አቶ አባ ዱላ ፥ ትምህርትና ቴክኖሎጂ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን ወሳኝ ነው ብለዋል።

ስንጀምር በ40ቀናት ውስጥ ሰርተን እናጠናቅቃለን ባልነው መሠረት ቃላችንን ጠብቀናል ፥ የኦሮሚያ ልማት ማህበር ትምህርት ቤቶችን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ግንባታዎችንም በ40 ቀን ውስጥ ሰርቶ አጠናቆ ለአገልግሎት እያበቃ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

የኦሮሚያ ልማት ማህበር ቀኝ እጃችን ነው ያሉት የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ቲጃኒ ናስር ፥ ትምህርት ቤት ከመገንባት በተጨማሪ የዞኑ ተማሪዎች ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ትልቅ ስራ ተሰርቷል ነው ያሉት።

በተመስገን አለባቸው

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!