የሀገር ውስጥ ዜና

በጤና ተቋማት ውስጥ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ ከአጋር ድርጅቶች ጋር እንሰራለን – ዶ/ር ሊያ ታደሰ

By Meseret Awoke

March 26, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጤና ተቋማት ውስጥ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ ከአጋር ድርጅቶች ጋር እንሰራለን ሲሉ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።

ዶክተር ሊያ ይህንን ያሉት ዛሬ በጅማ ዞን ሰቃ ጮቆርሳ ወረዳ የተለያዩ የጤና ተቋማትን በጎበኙበት ወቅት ነው።

የሰቃ ጮቆርሳ ሆስፒታልና ሌሎች የጤና ተቋማትን ሲጎበኙም ፥ የአንቡላንስና የህክምና መሳሪያዎች እጥረት በጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ችግር እየፈጠረ መሆኑን ባለሙያዎችና የሃገር ሽማግሌዎች ለሚኒስትሯ ገልጸውላቸዋል።

ዶክተር ሊያ በዚህ ወቅት እንዳሉት ፥ ችግሮቹ በሌሎች የጤና ተቋማት ውስጥ መኖራቸውንና አጋር ድርጅቶችን በማሳተፍ ለመቅረፍ ይሰራል።

ሚኒስትሯ አክለውም የጅማ ዞን ነዋሪዎች፣ አመራሮችና ባለሙያዎች የጤና ተቋማትን ለማስፋፋትና ለማሻሻል በቅንጅት እየሰሩ ላሉት ስራ አድናቆታቸውን ገልፀዋል።

በሙክታር ጠሃ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!