የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሚያ የባህል ሳምንት በሻሸመኔ ከተማ እየተካሄደ ነው

By Feven Bishaw

March 27, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ባህላችን ለቱሪዝም ዕድገታችን” በሚል መሪ ሀሳብ በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የባህል ሳምንት (ፌስቲቫል) በምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ እስከ መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል፡፡

በዚህም በጠዋቱ በጎዳና ላይ ትርዒት መከበር የጀመረ ሲሆን ÷ከክልሉ በተጨማሪ የሌሎች ክልሎች የባህል ቡድን አባላት በተጋባዥነት በባህል ሳምንቱ እየተሳተፉ ነው፡፡