ስፓርት

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከጋና አቻው ጋር የመልስ ጨዋታውን ያደርጋል

By Feven Bishaw

March 27, 2022

አዲስ አበባ፣መጋቢት 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከጋና አቻው ጋር የሚያደርገውን የመልስ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ያከናውናል።

በአሰልጣኝ ፍሬው ሀይለገብርኤል የሚመራው ብሄራዊ ቡድኑ ምሽት 12 ሰዓት ለሚካሄደው የመልስ ጨዋታ ወደ አክራ በማቅናት ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡