የሀገር ውስጥ ዜና

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክርቤት መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ

By Alemayehu Geremew

March 28, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክርቤት መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው፡፡

ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት በሚያካሂደው ጉባዔው÷ የ12ኛ መደበኛ ጉባዔ ቃለ ጉባዔ እና የክልሉን የአስፈጻሚ አካላት የ2014 ዓ.ም የ6 ወር ሪፖርት በማድመጥ መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረግን ጨምሮ በ8 የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን እንደሚያልፍም ይጠበቃል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን የክልሉን የአስፈጻሚ አካላት የ2014 ዓ.ም የ6 ወራት አፈጻጸም እያቀረቡ መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡