አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ላይ ትኩረቱን ያደረገ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
አካታች፣ ተደራሽ እና ጥራት ያለው ትምህርት፣ ሥደተኞች፣ ከሥደት ተመላሾችና ሥደተኛ ተቀብለው የሚያስተናግዱ ማኅበረሰቦች የሚያገኙበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር እና ሁኔታውን ማሳለጥ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከር የኮንፈረሱ ዋነኛ አጀንዳ ነው ተብሏል።
ኮንፈረንሱ በፈረንጆቹ ታኅሣሥ 2021 በጂቡቲ ተካሂዶ በነበረው ኮንፈረንስ ላይ በተቀመጡ አቅጣጫዎች ላይ የተገኙ ውጤቶች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።
በኮንፈረንሱ የኢጋድ አባል ሀገራት ተሳታፊ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።