ዓለምአቀፋዊ ዜና

ሩሲያ እና ዩክሬን የሰላም ድርድራቸውን ነገ በኦንላይን ሊቀጥሉ ነው

By Meseret Awoke

March 31, 2022

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ እና ዩክሬን የሰላም ድርድራቸውን ነገ በቀጥታ (ኦንላይን) ሊቀጥሉ ነው።

የዩክሬን ተደራዳሪ ዴቪድ አራካሚያ ሁለቱ ሃገራት በቱርክ ስኬታማ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውሰው፥ በነገው እለት በኦንላይን ቀጣይ ድርድራቸውን ያካሂዳሉ ብለዋል።

አያይዘውም ዩክሬን የሁለቱ ሃገራት መሪዎች ተገናኝተው የሚደራደሩበትን ሃገር በተመለከተ ሃሳብ ማቅረቧን አስታውቀዋል።

ይሁን እንጅ ከሩሲያ በኩል ሃገራቱ በሚገቡት የስምምነት ረቂቅ ላይ ተጨማሪ ስራ መሰራት አለበት የሚል ምላሽ መሰጠቱን ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ሩሲያ በማሪፑል ከዛሬ ጀምሮ የሚተገበር የተኩስ አቁም ይፋ አድርጋለች።

የተኩስ አቁሙ ንጹሃንን ከጦርነት ቀጠናው ለማስወጣት እንደሚረዳ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር መግለጹን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!