አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የረመዳን ወር ይቅር የምንባባልበት መሆኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ ገለጹ፡፡
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ የታላቁ ረመዳንን ወር ፆም አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል ።
ረመዳን ሙስሊሞች ራሳቸውን ከምግብና ከመጠጥ ብቻ የሚያርቁበት ወር ሳይሆን፥ ከአላህ ጋር የሚቀራርቡበትና የግል ስሜታቸውን እና ራስ ወዳድነታቸውን የሚያርቁበት ወር ነው ብለዋል ።
በመግለጫው የረመዳን ወር የበጎ አድራጎትና የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብርንም ይፋ አድርገዋል።
መርሃ ግብሩ ይፋ የተደረገው በአፍሪካ ህብረት አጠገብ ለመስጂድ ግንባታ በተከለለው ስፍራ ሲሆን ፥ ድጋፉን ለሚያደርጉ ሁሉ ምቹ ሁኔታ መዘጋጀቱም ተገልጿል።
በተለይ ወቅቱ በጦርነትና በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉ እንዲሁም ከሳዑዲ ተመላሽና ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ያሉበት በመሆኑ የተለያዩ አካላት ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል መርሃ ግብር መሆኑ ተጠቅሷል።
ረመዳን ሸይጣን የታሰረበትበትና ቁርዓን የወረደበት ወር መሆኑንም ገልጸዋል ።
ረመዳን ይቅር የሚባባሉበት ከ11 ወር ስህተታችን ወጥተን ወደ አላህ የምንቃረብበት፣ ያለው ለሌለው አካፍሎ የሚያበላበት የራህመት ወር ነውም ሲሉ ተናግረዋል።
በመሆኑም ሙስሊሞች በዚህ የተቀደሰ ወር ተጠቃሚ እንድንሆን ራሳችንን ማስተካከል ይጠበቅብናል ማለታቸውን የዘገበው ኢቢሲ ነው ።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!