የሀገር ውስጥ ዜና

15ኛው የስልጤ የባህል፣ የታሪክ እና ቋንቋ ሲምፖዚየም በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

April 01, 2022

አዲስ አበባ፣መጋቢት 23፣2014 (ኤፍ ቢሲ) 15ኛው የስልጤ የባህል፣ የታሪክ እና ቋንቋ ሲምፖዚየም በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

ከሲምፖዚየሙ በተጨማሪ በእለቱ በዞኑ የማንነት ጥያቄ የተመለሰበትን 21ኛ አመት ጎን ለጎን እየተከበረ ይገኛል፡፡

ሲምፖዚየሙ የደቡብ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ሰርሞሎ እና ሌሎች ከፍተኛ የክልል እና የዞን ባለስልጣናት በተገኙበት ነው እየተካሄደ ያለው።

የስልጤ ህዝብ ማንነት የተረጋገጠበት ቀን ክብረ በዓል ካለፈው መጋቢት 20 ቀን 2014 ጀምሮ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ የቆየ ሲሆን የዛሬው የመዝጊያ ስነ ስርዓት ነው።

ዛሬ እየተካሄደ ያለው የፓናል ውይይት በስልጤ ህዝብ ታሪክ፣ ቋንቋ እና ባህል ላይ ነው።

በፓናሉ ላይም የአከባቢው ተወላጆች እና ከዞኑ የተውጣጡ የተለያዩ እንግዶች እየተካፈሉም ይገኛሉ።

የዘንድሮው የስልጤ ህዝብ ማንነት የተረጋገጠበት 21ኛ ዓመት ሲሆን እየተከበረ ያለው፥ በዓሉ ሲከበር ዘንድሮ ለ15ኛ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ! ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!