አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት አመራሮች ወደ ሩሲያ እንዳይገቡ መታገዳቸውን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
በአመራሮቹ ላይ የተጣለው እገዳ ሞስኮ ዩክሬን ላይ ከወሰደችው ወታደራዊ እርምጃ ጋር በተያያዘ በምዕራባውያን ለተጣለባት ማዕቀብ የአጸፋ ምላሽ መሆኑን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
እገዳው በርካታ የአውሮፓ ኮሚሽነሮችን እና የአውሮፓ ህብረት ወታደራዊ መዋቅር ሃላፊዎችን እንዲሁም ፀረ-ሩሲያ ፖሊሲ የሚያራምዱ አብዛኞቹን የአውሮፓ ፓርላማ አባላትን ጨምሮ በአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ አመራሮች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል መባሉን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡
አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያን አገራት ሞስኮ በዩክሬን ላይ የወሰደችውን ወታደራዊ እርምጃ በመቃወም እና ከዩክሬን ጎን በመቆም ሩሲያ ላይ ማዕቀቦችን መጣላቸው ይታወሳል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!