የሀገር ውስጥ ዜና

በረመዳን ጾም ወቅት በጦርነትና በድርቅ የተጎዱ ወገኖችን ማሰብ ይገባል – ጠ/ሚ ዐቢይ

By Alemayehu Geremew

April 01, 2022

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በታላቁ የረመዳን ጾም ወቅት በጦርነትና በድርቅ የተጎዱ ወገኖችን ህዝበ ሙስሊሙ እንዲያስባቸው ጠይቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ጾም ራስን አጥርቶ የመመልከቻ ጊዜ መሆኑን አመላክተዋል።

“የረመዳን ወቅት ራሳችንንና ሀገራችንን በሚገባ የምናይበትና የጎደለንን የምንሞላበት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል።

የረመዳን ጾም በነገው እለት ይጀምራል።