የሀገር ውስጥ ዜና

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ቁምቢ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By Alemayehu Geremew

April 03, 2022

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 25 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ቁምቢ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ አስታወቀ።

የዞኑ ፖሊስ ኮሚሽን የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጐሹ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ዛሬ ረፋድ አራት ሰዓት አካባቢ የሠሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 -75091 ኦሮ የጭነት አይሱዙ የጭነት መኪና ከጎሎኦዳ ወረዳ ወደ ቁምቢ ወረዳ የተለያዩ ሸቀጦች እና 20 ሰዎችን ጭኖ ሲሄድ ተገልብጧል

በአደጋው የስድስት ሰዎች ሕይወት ወዲያው ሲያልፍ በ12 ሰዎች ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት በመድረሱ ለተጨማሪ ከፍተኛ ሕክምና ወደ በደኖ ሆስፒታል ተወስደዋል ብለዋል።

አደጋው ከአቅም በላይ በመጫን እና በከፍተኛ ፍጥነት ምክንያት መድረሱንም ተናግረዋል።

አሽከርካሪው ለጊዜው ከአባባቢው መሰወሩንና በወረዳው ፖሊስ አባላት ክትትል እየተደረገበት መሆኑን ገለፀዋል።

በተሾመ ኃይሉ