የሀገር ውስጥ ዜና

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀ የዓባይ ህብረ ዝማሬ እየተመረቀ ነው

By Meseret Awoke

April 07, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀ የዓባይ ህብረ ዝማሬ እየተመረቀ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው ያዘጋጀው ህብረ ዝማሬ ዋና ትኩረቱ የዓባይ ወንዝን በተመለከተ ከፍ ያለ ሃገራዊ ስሜት ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ተነግሯል።

ከህብረ ዝማሬው በተጨማሪ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ እና አለም ዓቀፍ የጥናት ማዕከል ማስጀመሪያ መርሃ ግብርም እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የጎንደር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አጸደ ወይን እና ሌሎች እንግዶች ታድመዋል።

በለይኩን ዓለም

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!