አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀንጋሪ የአውሮፓ ህብረት በሞስኮ ላይ የጣለውን የኃይል ማእቀብ ውድቅ በማድረግ የሩሲያን ነዳጅ በሩሲያ መገበያያ ገንዘብ ሩብል ለመግዛት ተስማምታለች፡፡
የሀንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን እንደተናገሩት ሀንጋሪ ከሩሲያ ጋር በምታደርገው የነዳጅ ግብይት በሩብል ለመክፈል መስማማቷን ተናግረዋል።
የአውሮፓ ህብረት በነዳጅ እና በጋዝ ላይ የጣለው ማዕቀብ ሀገሪቱ የማትሻገረው ቀይ መስመር ነበር በማለት ተቃውሟቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ሀንጋሪ የነዳጅ ግብይቱ ሩሲያ በፈለገችው መንገድ በሩብል ለማከናወን ዝግጁ ናት ማለታቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ብላድሚር ፑቲን በሞስኮ ለተጣለው የሀይል ማዕቀብ አጸፋ ምላሽ ለመስጠት አውሮፓውያን ከሩሲያ ጋር በሚያደርጉት የነዳጅ እና ጋዝ ግብይት በሩብል ካልከፈሉ ግብይት አይኖርም በማለት ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!