የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ህብረት የቢዝነስ ፎረም ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመች

By Melaku Gedif

April 07, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት ቢዝነስ ፎረም በኢትዮጵያ በቀጣይ ከመንግስት ጋር ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ቢዝነስ ፎረም ሊቀመንበር ሚስተር ቤን ዲፓራትሬ ከገንዘብ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ሰመሬታ ሰዋሰው ጋር የድርጅቱን የ2021 የስራ ድባብ ሪፖርትን ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው ስምምነቱን የተፈራረሙት፡፡

ሰመሪታ ሰዋሰው የኢትዮጵያ መንግስት ከአውሮፓ ቢዝነስ ፎርም ጋር የረጅም ጊዜ አጋርነቱን ለማጠናከር ፍላጉት እንዳለው ጠቅሰዋል፡፡

በተለይም ትብብሩ የግሉን ዘርፍ ኢንቨስትመንትን በማጎልበት ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለበት ያሳሰቡት ሚኒስትር ዴኤታዋ÷የመግባቢያ ስምምነቱ በመንግስትና በግሉ ዘርፍ መካከል የልምድ ልውውጥ እና የጋራ ምክክር እንዲኖር ያስችላል ብለዋል፡፡

መንግስት እየተገበረ ባለው ማሻሻያ የሎጀስቲክስ ዘርፍን ጨምሮ በመሠረተ ልማት አውታሮችን በመገንባት፣የሰው ሃይል አቅም በማሰደግ፣የቁጥጥር ማዕቀፉን በማሻሻል እና የግሉን ዘርፍ ለሚደገፉ ተቋማት መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

የአውሮፓ ቢዝነስ ፎረም በኢትዮጵያ ሊቀመንበር ሚስተር ቤን ዲፓራትሬ በበኩላቸው÷ የአውሮፓ ቢዝነስ ፎረም የግሉ ሴክተር ችግሮቹን ለመፍታት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ገንቢ እና ግልጽ ውይይት በማድረግ ችግሮች እንዲፍቱ ይሰራል ብለዋል፡፡

በአውሮፓ ኅብረት አነሳሽነት ታደጊ አገሮች ወደ አውሮፓ ህብረት የሚገቡት ምርቶች በሙሉ ከቀረጥ ነፃ እድል እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን መቀመጫቸውን ኢትዮጵያ ያደረጉ በርካታ ኩባንያዎችም እየተጠቀሙበት ይገኝሉ ሲሉ ገለፀዋል፡፡ የአውሮፓ ቢዝነስ ፎረም በኢትዮጵያ መሰረታቸውን አውሮፓ ባደረጉ ባለሀብቶች ተቋቁሞ ስራውን በፈረንጆቹ 2012 የጀመረ ሲሆን÷ ዋና አላማውም ኢትዮጵያን ለአውሮፓ ባለሀብቶች ተመራጭ መዳራሻ ማድረግ ነው፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱ በገንዘብ ሚኒስቴርና በግሉ ዘርፍ መካከል የተሻለ መቀራረብ ለመፍጠር፣ ጥሩ ልምዶችን ለማማሪያነት ለመጠቀም፣ በየወቅቱ የጋራ ምክክር ለማድረግ የሚያግዝ ነው መባሉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ የአውሮፓ ቢዝነስ ፎረም በኢትዮጵያ መሰረታቸውን አውሮፓ ባደረጉ ባለሀብቶች ተቋቁሞ ስራውን እ.አ.አ በ2012 የጀመረ ሲሆን፤ ዋና አላማውም ኢትዮጵያን ለአውሮፓ ባለሀብቶች ተመራጭ መዳራሻ ማድረግ ነው፡፡