የሀገር ውስጥ ዜና

ዜጎችን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው የመመለሱ ስራ ቀጥሏል

By Meseret Awoke

April 08, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በሁለት ዙር ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ህጻናትን ጨምሮ ሴቶች ተመልሰዋል፡፡

ዛሬ ማለዳ በተደረገው የመጀመሪያ በረራ 105 ህጻናት ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዛሬው ዕለት በመጀመሪያው በረራ ከጂዳ 441ዜጎች የተመለሡ ሲሆን ፥ ከነዚህ መካከል 105 ህጻናት ሲሆኑ የተቀሩት 336ቱ ሴቶች ናቸው፡፡

በሁለተኛው በረራ 409 ዜጎች ከጂዳ የተመለሱ ሲሆን ፥ ከነዚህ መካከል 211 ህጻናት ሲሆኑ ፥ የተቀሩት 198ቱ ሴቶች መሆናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም በተደረገው ሦስተኛ በረራ ከሳዑዲ አረቢያ 472 ሰዎች ሲመለሱ ፥ 128ቱ ህጻናት ሲሆኑ የተቀሩት 344 ሴቶች ናቸው፡፡ መንግስት ዜጎችን ወደ ሀገር በመመለስ የተለያዩ ድጋፎችን እንዲያገኙ እያደረገ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፥ ዜጎችን ወደአገራቸው የመመለሱ ስራ 11ኛ ቀኑን ይዟል፡፡

በዚህም መንግስት በሳዑዲ አረቢያ በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚመራና 16 መንግስታዊ መስሪያ ቤቶችን በአባልነት ያቀፈ ብሔራዊ ኮሚቴ በማዋቀር 102 ሺህ ዜጎችን ወደ ሃገር ለመመለስ በማቀድ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል ።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!