የሀገር ውስጥ ዜና

በድሬዳዋ ከተማ 10 ሚሊየን ብር የሚገመቱ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

By Meseret Awoke

April 08, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ አስተዳደር 10 ሚሊየን ብር የሚገመቱ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸው ተገለጸ።

በድሬዳዋ ከተማ ውስጥ ሰርጎ በማስገባት ተደብቀው የነበሩ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውንና እንደተቻለና በቁጥጥር ስር የዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎችም እስከ 10 ሚሊየን ብር እንደሚገመቱ በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ስራ-አስኪያጅ አቶ ደመላሽ ተሾመ ገልጸዋል።

ለሀገር የሚውለውን ሀብትና ንብረት በግለሰቦች ስር ሆኖ መቀመጡ ህገወጥነት እንደሆነና ሁሉም ህገ-ወጥ የሆኑ ንግዶች ወደ ተስተካከለ የንግድ ስርዓት ሊገቡ እንደሚገባ በጉምሩክ ኮሚሽን የተቋማዊ ስጋት ስራ አመራርና ሥነ-ምግባርዳይሬክተር ወይዘሮ ሰርካለም አበበ ተናግረዋል ።

በቀጣይ በኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎች ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠትና በመስራት እርምጃ የመውሰድ ስራዎች እንደሚጠናከሩና ለነዚህም ስራዎች መሳካት ህብረተሰቡ ከፀጥታ ሀኃይሎች ጋር በጋራ በመሆን መስራት እንደሚገባቸው በፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ የኮንትሮባንድ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ የሬጅመንት አንድ አዛዥ ኮማንደር ስለሺ በየነ አሳሰበዋል።

በከተማዋ የተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች በአብዛኛው የተለያዩ መድሃኒቶች ፣ ጨርቃ-ጨርቆች ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ እንዲሁም የመኪና መለዋወጫዎች እንደሆኑም ከከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!