አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስቴር መሰረታዊ የምግብ ሽቀጦች የሆኑት ዘይት፣ ስንዴ፣ ስኳር፣ የህጻናት ወተት እና ሩዝ ያለምንም የውጭ ምንዛሬ ፍቃድ (በፍራንኮ ቫሉታ) በጉምሩክ ኮሚሽን በኩል በቀጥታ እንዲገቡ ወሰነ፡፡
መንግስት በአሁኑ ወቅት እየተስተዋለ ያለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት እንዲቻል እና በርካታ የውጭ ሀገር የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ኢትዮጵያዊያን የራሳቸውን ሚና መጫወት እንዲችሉ የፍራንኮ ቫሉታ ፈቃድ በተፋጠነ ሁኔታ እንዲፈቀድላቸው ጥያቄ እያቀረቡ በመሆኑ መወሰኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
ቀርጥና ታክስን በሚመለከት በገንዘብ ሚኒስቴር በ22/3/2013 ዓ.ም በቁጥር ማአ.30/7/51 በተጻፈው ደብዳቤ መሰረት እንዲፈጸም ፤ አፈጻጸሙን በተመለከተ ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት በኩል ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንዲደረግበት መወሰኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!