የሀገር ውስጥ ዜና

የአፋር ክልል የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ ይፋ ሆነ

By ዮሐንስ ደርበው

April 09, 2022

የአፋር ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ያሲን ሀቡብ የጤና ኤክስቴንሽን ማሻሻያ ፍኖታ ካርታው እስትራቴጂክ እቅድ በክልሉ እውን ለማድረግ እንደሚሰሩ ገልጸው÷ ፕሮግራሙ 18ቱን የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆች ህብረተሠቡ እንዲጠቀም በማድረግ የራሱን ጤና በራሱ መጠበቅ እንዲችል የሚያግዝ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በተጨማሪም የክልሉ የጤና ሥራዎች በጥናት ላይ ተመስርተው እንዲሠሩ ከአርማወር ሀንሰን የምርመር ተቋም ጋር የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

የአርማወር ሀንሰን የምርምር ተቋም ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ÷ በክልሉ የአርብቶ አደር ጉዳዮችን ለመረዳት እና ለመስራት የተቋሙ ሙያተኞች ወደ ክልሉ ሲመጡ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡