የሀገር ውስጥ ዜና

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ልዑካን ከቱርክ ተቋማት ጋር የልምድ ልውውጥ እያደረጉ ነው

By Melaku Gedif

April 11, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ልዑካን ቡድን ከቱርክ አቻ ተቋማት ጋር የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ቱርክ አንካራ ገብቷል፡፡

በባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ የሚመራው የልዑካን ቡድኑ÷በቱርክ አንካራ ከተማ ከሚገኙ መንግስታዊ ተቋማት ጋር ለአምስት ቀናት የሚቆይ የልምድ ልውውጥ እንደሚያካሂድ ተገልጿል፡፡

የልምድ ልውውጡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለሚቀጥሉት አስር አመታት የሚመራበትን የስትራቴጂክ ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማዘጋጀት ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ልዑክ ቡድኑ በዛሬው ዕለት በነበረው ፕሮግራም መሰረትም ከአንካራ ማህበራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ጋር በአገሪቱ የሲቪክ ማህበራት እና በጎ አድራጎት ድርጅቶች አደረጃጀት፣ ክትትል እና ድጋፍ ላይ ያተኮረ የልምድ ልውውጥ አካሂደዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በቀጣይ 3 ቀናት ሌሎች የቱርክ ተቋማት ጋር ተጨማሪ የልምድ ውውጥ ፕሮግራም ያካሂዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ! ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!