አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ”ኤች አር 6600” እና የ”ኤስ 3199” ረቂቅ ሕጎች የሚቃወም ሰልፍ በካሊፎርኒያ ግዛት ሎስ አንጀለስ ከተማ ተካሄደ።
ሰልፉ የተካሄደው የ”ኤችአር 6600” ረቂቅ ሕግን በተባባሪነት ያዘጋጁት የካሊፎርኒያ የኮንግረስ አባል ብራድ ሼርማን ቢሮ ፊት ለፊት ነው።
በሰልፋ ላይ ኢትዮጵያውያን፣ ኤርትራውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች “ኤች አር 6600” እና “ኤስ 3199 ረቂቅ ሕጎች” እንደሚቃወሙትና ሕጎቹ ኢትዮጵያን እንዲሁም በኢትዮጵያና አሜሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚጎዳውን ሕግ ውድቅ እንዲደረግ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
“ማዕቀብ ይገድላል ይጎዳል “፣”ረቂቅ ሕጎቹ የምስራቅ አፍሪካን ሰላምና መረጋጋት አደጋ ላይ የሚጥሉ ናቸው” እና ሕጎቹ በየትኛውም ዓይነት ሁኔታ የኢትዮጵያንና አሜሪካን ጥቅምና ፍላጎት አያስጠብቁም” የሚሉ መፈክሮች በሰልፉ ተደምጠዋል።
“ኤች አር 6600” እና “ኤስ.3199” ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ ዋይት ሃውስ ፊት ለፊት መካሄዱ የሚታወስ ነው።
የኤችአር 6600′ አጋዥ የሆነው ‘ኢትዮጵያን ፒስ ኤንድ ዴሞክራሲ ፕሮሞሽን አክት ኦፍ 2022’ ወይም ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕግ በኒውጀርዚ ሴናተር ሮበርት ሜኔንዴዝ አርቃቂነት የተዘጋጀ ሲሆን ፥ ሴኔቱ እ.አ.አ በ2022 ሊመለከታቸው በጊዜ ሰሌዳው ከያዛቸው ረቂቅ ሕጎች አንዱ ሆኖ እንዲካተት መወሰኑ ይታወሳል።
በአሜሪካ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ረቂቅ ሕጎቹ በሕግ አውጪው አካል ድምጽ ተሰጥቶባቸው እንዳይጸድቁ ለማድረግ ሴናተሮችና የኮንግረስ አባላትን በማናገር፣ ደብዳቤ በመጻፍ፣ ፊርማ በማሰባሰብና በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ዘመቻ በማድረግ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ኢዜአ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!